logo

የጨቅላ ህጻናት አመጋገብ

ምግብ እንዴት ይጀመራል?

የምንመርጠው የምግብ አይነት ጤናማ መሆን እና ከተለያየ የምግብ አይነት የተሰራ መሆን አለበት አትክልትና ፊራፍሬን ጨምሮ ምንም አይነት ጨው አለመጨመር።ለስለስ ያሉና መታኘክ የማያስፈልጋቸው መሆን አለባቸው። የአለርጂ ችግር ካልታየባቸው ከ ማር ዉጪ ማነኛውም ምግብ መመገብ እንቺላለን። ምግብ ቀስ በቀስ አይነቱን እና መጠኑን እየጨመሩ መሄድ።

በየስንት ጊዜው መመገብ አለብን?

ጨቅላ ህጻናት ከእናት ጡት በተጨማሪ ምግብ መውሰድ ሲጀምሩ በትንሽ መጠን መሆን አለበት የዕናት ጡት ወተትም ማቆም የለባቸውም ። መጠኑም ከ 6 ወር በፊት ከነበረው የእናት ጡት ወተት ወይም (Formula milk) በቀን ሁለት ጊዜ በ ጠጣር ምግቦች መቀየር

ህጻናት የመመገቢያ ክፍለ ጊዜ
እድሜ በወራትበ24 ሰአት ዉስጥ አማካይ የመመገቢያ ክፍለ ጊዜአማካይ የወተት መጠን በአንድ ጊዜ
የመጀመሪያ 2 ወራትየእናት ጡት ወተት ወይም Formula milk ብቻከ10-12 ጊዜ150ሚሊ ሊትር
3 እስከ 4 ወራትየእናት ጡት ወተት ወይም Formula milk ብቻከ 8-9 ጊዜ150ሚሊ ሊትር
5 እስከ 6 ወራትከ4-5 ጊዜ የእናት ጡት ወይም Formula milk እና 1 ወይም 2 ልዩጠጣርምግብ150ምሊሊትር እስከ 180 ሚሊ ሊትር
bf
የእንቅልፍ ክፍለ ጊዜ ከወሊድ እስከ 6 ወር
የጨቅላው እድሜ በወራትየእንቅልፍ ጊዜ በቀኑ ዉሎ ሰአት ዉስጥየእንቅልፍ ሰአት በማታ
ከወሊድ እስከ 2 ወርከ8-10 ሰአት7-9 ሰአት
ከ3እስከ 4ወርከ6-8 ሰአት8-10 ሰአት
5 እስከ 6 ወራትከ4-6 ሰአት8-10 ሰአት

ጤናማ የጨቅላ ህፃናት የሽንት እና ሰገራ

  • በተወለዱ በመጀመሪያወቹ ቀናት በቀን ውስጥ ከ6-8 ጊዜ ሽንት ይኖራቸዋል ቀለሙም ነጣ ካለ እስከ ደማቅ ቢጫ ሊሆን ይችላል።
  • በመጀመሪያ ቀናት የሚኖራቸው እያንዳንዱ ህፃን የተለያየ ቀለም ፡መጠን ፡ለስላሳና ወፍራምነት ይታያል።የእናት ጡት ወተት የሚጠቀሙ Formula milk ከሚጠቀሙ ነጣ እና ለስለስ ያለ ሰገራ ይኖራቸዋል።
  • የመጀመሪያ ሳምንት ፣ አንድ ጨቅላ ህፃን በቀን ዉስጥ ከ5 እስከ 10ጊዜ ሰገራ ሊኖረው ይችላል። ይህም ጠቆር ያለ፡ አረንጓዴ(ጎምኔ) መሰል ደረቅ ያለ ይሆናል ከዚያም ቢጫ ብሎም ወደ ቡናማ ቀለም እየተቀየረ ይሄዳል።
  • ከ 6ሳምንታት በኋላ ሰገራ የሚወጣበት ድግግሞሽ እየቀነሰ ይመጣል ማለትም በቀን ከአንድ ጊዜ በታች ሊሆን ይችላል።ቀለሙም በአብዛኛው ቢጫ ቀለም እየሆነ ይሄዳል።
  • ጨቅላ ህፃናት ከእናት ጡት ዉጪ ምግብ ከጀመሩ በኋላ ማለትም 6 ወር አካባቢ የሰገራ ዉፍረት እየጨመረ እና ጠረን ማምጣትም ይጀምራል።

ሃኪም ማማከር የሚያስፈልገው መቼ ነው?

  • የህፃኑ ሰገራ ቀለም ደም፡በጣም ጠቆር ያለ፡ነጭ ወይም ግራጫ ሲሆን
  • ሌሎች የአንጀት ህመም ምልክቶች ሲያሳይ ማለትም እንደ ማስመለስ
  • የሰገራ መድረቅ እና ለማሶጣት መጨነቅ ካሳዩ
  • በጣም ዉሃማ ሰገራ ከሆነ
ወደ ሐኪም