logo

የተለመዱ ችግሮች

ከፍተኛ የቅሪት ትዉከት

ከፍተኛ የቅሪት ትዉከት ማለት በእርግዝና የመጀመሪያ 20ሳምንታት የሚከሰት ከመጠን ያለፈ የማቅለሽለሽ እና ማስመለስ በሽታ ነው።

ምልክቶቹ

  • በቀን ዉስጥ በተደጋጋሚ የሚከሰት ማቅለሽለሽ እና ትዉከት
  • ከፍተኛ የድካም ስሜት
  • የሰውነት ክብደት መቀነስ
  • የደም ግፊት መጠን መቀነስና የልብ ምት መጨመር

ሕክምናዎች

  • የአኗኗር ዘይቤን መቀየር ፣ህመሙን የሚቀሰቅሱ ነገሮች ማሶገድ ሽታ፡ቦታወይም ድምፅ ፣የሚስማማ ምግብ መምረጥ፣ በቂ ፈሳሽ መውሰድ፣ዝንጅብል መጠቀም፣ የሚወስዱትን ምግብ እና ፈሳሽ መጠን ማሳነስ እና ቶሎ ቶሎ ትንሽ ምግብ መዉሰድ
  • ከዚህ ያለፈ የህመም ስሜት ሲኖር በጤና ተቋም ዉስጥ የሚደረጉ ህክምናወች -በደም ስር የሚሰጡ ፈሳሽ፣ ቫይታሚኖች፣አልሚ ምግቦች፣ እንዲሁም በሃኪም የሚታዘዙ ማስታወክና ማቅለሽለሽ የሚቀንሱ መድሃኒቶች መጠቀም።
ድንገተኛ የፅንስ መቋረጥ

ድንገተኛ የፅንስ መቋረጥ የምንለው ፅንስ ከተፈጠረ ከ 28 ሳምንታት በፊት የሚከሰት ድንገተኛ ውርጃ ነው።ይህም ከአጠቃላይ እርጉዝ እናቶች ዉስጥ 30% የሚሆኑት ላይ የሚከሰት ክስተት ነው።

ምልክቶቹ

  • ድንገተኛ የማህፀን ደም መፍሰስ
  • ከፍተኛ የሆድ ቁርጠት
  • የታችኛው የሆድ ክፍል ህመም

ሕክምናዎች

  • የፅንስ መቋረጥ ከተከሰተ በኋላ ድንገተኛ ህክምና
  • የስነልቦና ህክምና መስጠት
  • 3 ጊዜ እና ከዛ በላይ ከተከሰተ ስር የሰደደ ምርመራ እና ህክምና ያስፈልጋል።
የእርግዝና ወቅት ስኳር

የእርግዝና ወቅት ስኳር በእርግዝና ሰዓት የሚከሰት የስኳር አይነት ሲሆን ለመጀመሪያ ጊዜ በእርግዝና ወቅት የምርመራ የሚገኝ ነው።

ምልክቶቹ

  • የውሃ ጥም
  • የሽንት መብዛት
  • የምግብ ፍላጎት በከፍተኛ ሁኔታ መጨመር

ሕክምናዎች

  • የአኗኗር ዘዬ መቀየቀር ፦ ማለትም በእርግዝና ወቅት የሚፈቀዱ መጠነኛ እንቅስቃሴዎችን መድረግ፣ ጣፋጭ ምግቦችን በመተው አልያም በመቀነስ የደም ስኳርን መቆጣጠር ይቻላል።
  • የአኗኗር ዘዴ በመቀየር ካልተስተካከለ ወይም በሃኪምሽ ከታመነበት መርፌ ወይም ኪኒን በመጠቀም የደም ስኳርሽ ማስተካከል ይቻላል።
የእርግዝና ወቅት ግፊት

የእርግዝና ወቅት ግፊት ማለት፣ በእርግዝና ጊዜ በሚከሰት ከፍተኛ የደም ግፊት የተነሳ አንዳንድ ጊዜ በሰውነት ውስጥ የውሀ መጠራቀም እና በሽንት ውስጥ ፕሮቲን ሲኖር ይህም ከ20 ሳምንት ጀምሮ እሰከ ወሊድ ብሎም ስድስት ሳምንት የሚደርስ የግፊት አይነት ነው።

ምልክቶቹ

  • የእራስ ምታት ሕመም
  • የእይታ መለወጥ
  • ማቅለሽለሽ ፣የሆድ ሕመም የመሳሰሉት ስሜቶች

ሕክምናዎች

  • የግፊቱ መንስኤ እንግደልጁ እና ፅንሱ ስለሆኑ መደበኛ የግፊት መድሃኒቶች መጠቀም ጉዳቱ ያመዝናል ስለሆነም ፅንሱ እንዲወለድ ማድረግ ችግሩ ከመሰረቱ መፍታት ያስፈልጋል።
  • የመውለጃ ጊዜ ገና ከሆነና ሃኪሞች በጥንቃቄ መርምረው ከወሰኑ ለተወሰነ ጊዜ ሆስፒታል በመተኛት ጥብቅ ክትትል እና ህክምና ሊደረግ ይችላል።