ከፍተኛ የቅሪት ትዉከት
ከፍተኛ የቅሪት ትዉከት Hyperemesis Gravidarum ምንድን ነዉ? ከፍተኛ የቅሪት ትዉከት ማለት በእርግዝና የመጀመሪያ 20 ሳምንታት የሚከሰት ከመጠን ያለፈ የማቅለሽለሽ እና ማስመለስ በሽታ ነው። በእርግዝና ወቅት እስከ 16 ወይም 18 ሳምንታት በአብዛኛው ነፍሰጡር እናቶች ላይ ይህ ስሜት ቢኖርም ከፍተኛ የቅሪት ትዉከት ግን እስከ 2% የሚሆኑ ነፍሰጡሮችን ያጠቃል። ከፍተኛ የቅሪት ትዉከት ምልክቶች፣
ምክንያት
በአብዛኛው አይታወቅም ነገር ግን የእርግዝና ሆርሞን ማለትም HCG እና Estrogen መጨመር ጋር በተያያዘ፣ከአንድ በላይ ፅንስ እርግዝና፣ያልተለመደ የእንግዴ ልጅ የእርግዝና አይነት፣ ከዚ በፊት የነበረ የመኪና ጉዞ ህመም Motion sickness ፣ የቤተሰብ ተመሳሳይ ህመም ታሪክ፣ በቀድሞ እርግዝና ተመሳሳይ ህመም መኖር እና የመሳሰሉት።
ምልክት
- በቀን ዉስጥ በተደጋጋሚ የሚከሰት ማቅለሽለሽ እና ትዉከት
- ከፍተኛ የድካም ስሜት
- የሰውነት ክብደት መቀነስ
- የደም ግፊት መጠን መቀነስና የልብ ምት መጨመር
- የትንፋሽ ጠረን መቀየር
- የሰዉነት ድርቀት
- የሽንት መጠን መቀነስ እና የተለያዩ የኩላሊት በሽታ ምልክቶች
ሕክምና
- የአኗኗር ዘይቤን መቀየር ፣ህመሙን የሚቀሰቅሱ ነገሮች ማሶገድ ሽታ፡ቦታወይም ድምፅ ፣የሚስማማ ምግብ መምረጥ፣ በቂ ፈሳሽ መውሰድ፣ዝንጅብል መጠቀም፣ የሚወስዱትን ምግብ እና ፈሳሽ መጠን ማሳነስ እና ቶሎ ቶሎ ትንሽ ምግብ መዉሰድ
- ከዚህ ያለፈ የህመም ስሜት ሲኖር በጤና ተቋም ዉስጥ የሚደረጉ ህክምናወች -በደም ስር የሚሰጡ ፈሳሽ፣ ቫይታሚኖች፣አልሚ ምግቦች፣ እንዲሁም በሃኪም የሚታዘዙ ማስታወክና ማቅለሽለሽ የሚቀንሱ መድሃኒቶች መጠቀም።
ወደ ሐኪምድንገተኛ የፅንስ መቋረጥ
ድንገተኛ የፅንስ መቋረጥ የምንለው ፅንስ ከተፈጠረ ከ 28 ሳምንታት በፊት የሚከሰት ድንገተኛ ውርጃ ነው።ይህም ከአጠቃላይ እርጉዝ እናቶች ዉስጥ 30% የሚሆኑት ላይ የሚከሰት ክስተት ነው።
ምክንያት
- የእናት የጤና ችግር የውስጥ ደዌ ወይንም የማህፀን ችግር ሊሆን ይችላል
- የእንግዴ ልጅ ወይም የማህፀን አቀማመጥ
- አጋላጭ ነገሮች መኖር ፣ከመጠን ያለፈ ውፍረት ፡የታወቀ በሽታ፡
- የእናት እድሜ 35 እና ከዛ በላይ መሆን፡ መድሃኒቶች እና አደንዛዥ እፆች መጠቀም
- የእናት የሰውነት ክብደት አነስተኛ መሆን
ምልክት
- ድንገተኛ የማህፀን ደም መፍሰስ
- ከፍተኛ የሆድ ቁርጠት
- የታችኛው የሆድ ክፍል ህመም
ሕክምና
- የፅንስ መቋረጥ ከተከሰተ በኋላ ድንገተኛ ህክምና
- የስነልቦና ህክምና መስጠት
- 3 ጊዜ እና ከዛ በላይ ከተከሰተ ስር የሰደደ ምርመራ እና ህክምና ያስፈልጋል።
መከላከል
- ሙሉ በሙሉ መከላከል ባይቻልም ቅድመ እርግዝና እና ቅድመ ወሊድ ክትትል ማድረግ
- ቅድመ እርግዝና ቫይታሚን መዉሰድ
- ጤናማ የአኗኗር ዘይቤ መከተል
- የካፊን መጠን መቀነስ
- ቀለል ያለ የዘወትር የአካል ብቃት እንቅስቃሴ
ወደ ሐኪምየእርግዝና ወቅት ስኳር
የእርግዝና ወቅት ስኳር በእርግዝና ሰዓት የሚከሰት የስኳር አይነት ሲሆን ለመጀመሪያ ጊዜ በእርግዝና ወቅት የምርመራ የሚገኝ ነው። ስኳር በአራት ዋናዋና አይነቶች ያሉት ሲሆን የእርግዝና ወቅት ስኳር አራተኛው አይነት ስኳር በመባል ይታወቃል።
ምክንያት
- የሆርሞን አለመመጣጠን በእርግዝና ወቅት የእንግደልጅ እጅግ በጣም ብዙ ሆርሞኖችን የሚያመነጭ ሲሆን ከእነዚህም PLG (plasental lactogen )አንዱ ነው። ይህም ሆርሞን ኢንሱሊን በህዋሳት ወስጥ እንዳይሰራ በማደናቀፍ የደም ውስጥ ስኳር እንዲጨምር ያደርጋል።
- አካባቢያዊ ተፅኖ በእርግዝና ወቅት የክብደት መጨመር ህዋሳቶች ለኢንሱሊን ሆርሞን እንዳይታዘዙ ሊያደርግ ይችላል የሚል ሌላ መላምትም አለ።
ምልክት
- የውሃ ጥም
- የሽንት መብዛት
- የምግብ ፍላጎት በከፍተኛ ሁኔታ መጨመር
- የልጅ መፋፋት
- የእንሽርት ውሃ መብዛት
- የፅንስ ያፈጣጠር ችግር
ሕክምና
- የአኗኗር ዘዬ መቀየቀር ፦ ማለትም በእርግዝና ወቅት የሚፈቀዱ መጠነኛ እንቅስቃሴዎችን መድረግ፣ ጣፋጭ ምግቦችን በመተው አልያም በመቀነስ የደም ስኳርን መቆጣጠር ይቻላል።
- የአኗኗር ዘዴ በመቀየር ካልተስተካከለ ወይም በሃኪምሽ ከታመነበት መርፌ ወይም ኪኒን በመጠቀም የደም ስኳርሽ ማስተካከል ይቻላል።
- የስኳር ህመም ውስብስብ ጉዳቶች እንዳይከሰቱ ቁርስ ከመብላት በፊትና በማንኛውም ጊዜ ምግብ ከተበላ ከሁለት ሰዓት በኋላ የስኳር መጠንን መለካት
- ከፍተኛ የስኳር መጠን ከታየ ደግሞ ሆስፒታል ተኝተሽ ጥብቅ የፅንስ ክትትል እና የስኳር ልኬት ሊደረግልሽ ይችላል።
መከላከል
- ከእርግዝና በፊት ክብደት ማስተካከል
- ጤነኛ የአኗኗር ዘዴን መከተል
- ጤናማ የአኗኗር ዘይቤ መከተል
- አደገኛ አመጋገብ በማስቀረት (ጣፋጭ ፣ አልኮሆል፣ ጮማ እና ጨው) በመተው
- ጭንቀት ማስወገድ
- በቂ ውሃ በመጠጣት እና በቂ እረፍት በማድረግ) ስኳር እና ሌሎች ቋሚ ህመሞችን መከላከል ይቻላል
ወደ ሐኪምየእርግዝና ወቅት ግፊት
የእርግዝና ወቅት ግፊት ማለት፣ በእርግዝና ጊዜ በሚከሰት ከፍተኛ የደም ግፊት የተነሳ አንዳንድ ጊዜ በሰውነት ውስጥ የውሀ መጠራቀም እና በሽንት ውስጥ ፕሮቲን ሲኖር ይህም ከ20 ሳምንት ጀምሮ እሰከ ወሊድ ብሎም ስድስት ሳምንት የሚደርስ የግፊት አይነት ነው።
ምክንያት
- የመጀመሪያ እርግዝና
- እድሜ ከ35 በላይ መሆን
- የስኳር ህመም
- የመንታ ልጅ እርግዝና
- ውፍረት
ምልክት
- የእራስ ምታት ሕመም
- የእይታ መለወጥ
- ማቅለሽለሽ ፣የሆድ ሕመም የመሳሰሉት ስሜቶች
ሕክምና
- የግፊቱ መንስኤ እንግደልጁ እና ፅንሱ ስለሆኑ መደበኛ የግፊት መድሃኒቶች መጠቀም ጉዳቱ ያመዝናል ስለሆነም ፅንሱ እንዲወለድ ማድረግ ችግሩ ከመሰረቱ መፍታት ያስፈልጋል።
- የመውለጃ ጊዜ ገና ከሆነና ሃኪሞች በጥንቃቄ መርምረው ከወሰኑ ለተወሰነ ጊዜ ሆስፒታል በመተኛት ጥብቅ ክትትል እና ህክምና ሊደረግ ይችላል።
መከላከል
- በሃኪም የሚታዘዙ መድሃኒቶችን(አስፕሪንና ካልሺየም) በጥንቃቄ በመውሰድ
- ስኳርና ግፊትን በመቆጣጠር
- አጋላጭ ሁነቶችን በመቀየር ማለትም ከመጠን ያለፈ ክብደትን በማስተካከል
ወደ ሐኪምየድህረ ወሊድ ደም መፍሰስ
በምጥ ለወለደች እናት >500ሚሊ ፥በቀዶ ህክምና ለወለደች >1000ሚሊ እንዲሁም መንታ እርግዝና ከነበረ >1500ሚሊ በላይ ደም ከፈሰሳት ነው።ምን ያህል እንደደማች በትክክል ማወቅ በጣም አስቸጋሪ ነው። ስለዚህ ሌሎች ምልክቶችን ማስተዋል ያስፈልጋል።
ምክንያት
- የማህጸን ልል መሆን
- የእንግዴ ልጅ በከፊል ማህጸን ውስጥ መቅረት
- የማህጸንና የመራብያ አካላት ጉዳት
- የደም መርጋት ችግር
አጋላጭ ሁኔታዎች ምን ምን ናቸው?
- መንታ እርግዝና
- በእርግዝና ጊዜ የሚከሰት ከፍተኛ የደም ግፊት
- የጽንሱ ክብደት መተለቅ
- በምጥ መርፌ መውለድ
አንዲት እናት ከፍተኛ የደም መፍሰስ ሲያጋጥማት ምን ማድረግ አለብን?
- መንስኤውን ለይቶ ማወቅና አስፈላጊውን እርዳታ ማድረግ
- የደም ማቆምያ መድሃኒቶችን እንዳስፈላጊነቱ መስጠት
- በህክምና እርዳታ ደሙን ማቆም ካልተቻለ በቀዶ ህክምና ማህጸን እስከ መውጣት ሊያደርስ ይችላል።
- የደም ናሙና መውሰድና ተመሳሳይ የደም አይነት ማዘጋጀት እና እንዳስፈላጊነቱ መስጠት
መከላከል
- በወሊድ ጊዜ የሚከሰት ከፍተኛ የደም መፍሰስ ከቀላል የደም ማነስ እስከ ሞት ሊያደርስ የሚችል በመሆኑ ተገቢውን የጤና ክትትል ማድረግና በጤና ተቋም መውለድ አስፈላጊ ነው።
ወደ ሐኪምስለ ድህረ ወሊድ ጭንቀት፥ድባቴ እና ሳይኮሲስ
የድህረ ወሊድ ጭንቀት ወይም የሃዘን ስሜት በመጀመርያዎቹ የወሊድ ሳምንታት በብዙ እናቶች ላይ የሚከሰት ችግር ሲሆን በሆርሞን መዛባትና የኑሮ ለውጥ ምክንያት የሚመጣ ነው። ከምልክቶቹም መካከል የሃዘን ስሜት፥መነጫነጭ፥የስሜት መለዋወጥ፥ማልቀስ ጥቂቶቹ ሲሆኑ ቀላልና እስከ 2 ሳምንት ባለው ጊዜ በራሱ የሚስተካከል (self limiting)ነው።
የድህረ ወሊድ ድባቴ
በመጀመሪያዎቹ የወሊድ ወራት ላይ የሚከሰት የአእምሮ ጤና ችግር ሲሆን ከወሊድ በኋላ የሚኖሩ የሆርሞን እና የሰውነት ለውጦች ከሌሎች የአእምሮ እና ማህበራዊ ጫናዎች ጋር አንድ ላይ በመሆን ከወሊድ በኋላ የሚከሰት ድባቴ (Postpartum Depression) ሊያመጡ ይችላሉ። ከ 10-15% የሚሆኑ እናቶች ከወሊድ በኋላ የድባቴ (depression) ተጠቂ ናቸው።
ምልክት
- ከልክ በላይ የሆነ የድብርት ስሜት፣ መከፋት
- ከፍተኛ የድካም ስሜት
- የምግብ ፍላጎት መቀነስ፣ የእንቅልፍ ማጣት
- ከተወለደው ህፃን ጋር ለመናበብና ለመቀራረብ መቸገር
- ከቤተሰብ ጋር መግባባት አለመቻል
የድህረ ወሊድ ሳይኮሲስ
ከወሊድ በኋላ አልፎ አልፎ የሚከሰት(rare) ነገር ግን ከፍተኛ የአእምሮ ጤና ችግር
ምልክት
- ለሌሎች የማይታዩና የማይሰሙ ነገሮችን ማየትና መስማት
- የሌሉ ነገሮችን አሉ ብሎ ማሰብ ወይም ከንቱ ስሜት
- ከፍተኛ የስሜት መለዋወጥ
ወደ ሐኪምሾተላይ
ሾተላይ የተባለው በሽታ በእናትና ፅንስ የደም አይነት አለመጣጣም ምክንያት የሚከሰት ከሁለተኛ ጀምሮ የሚወለዱ ህፃናትን የሚያጠቃ በሽታ ነው።
ምክንያት
- ሾተላይ የሚከሰተው የእናትየው የደም አይነት RH negative፣ የአባትየው የደም አይነት RH positive እና የፅንሱ የደም አይነት ደግሞ RH positive ሲሆን እንዲሁም በተለያዩ ምክንያቶች የፅንሱ ደም ወደ እናትየው ደም ከተቀላቀለ ነው።
- RH positive የምለው አራቱ የደም አይነቶች ማለትም A፣B፣AB እና O ሲሆኑ በሰዉነት ዉስጥ የሚገኙ የቀይ የደም ህዋሶች(RBCs) የላይኛው ሽፋናቸው ላይ Rh የተባለ ፕሮቲን ካላቸው ነው ማለትም A+፣B+፣AB+፣O+ ይሆናል።RH negative የምንለው ደግሞ በተቃራኒው RH ፕሮቲን የሌላቸው A-፣B-፣AB-፣O- ይሆናሉ።
- አንዲት ሴት ሾተላይ የሚባለው ችግር ሊከሰትባት የሚችለው እሷ Rh negative ሆና በተለያዩ አጋጣሚዎች Rh positive የሆነ ደም ወደሰውነቷ ሲገባ ሰውነቷ እነኚህን Rh positive የደም አይነቶች የሚያጠፉ(የሚገሉ) ንጥረ ነገሮች (Abs) ሲያመርት ነው። እነኚህም እስከ እድሜልክ በሰውነቷ ይቆያሉ።
- እነኚህ የተመረቱት ተከላካይ ንጥረ ነገሮች(Antibodies) የመጀመሪያው ልጅ ላይ ምንም ተፅዓኖ ሳይኖራቸው ልጁ በሰላም ሊወለድ ይችላል ነገር ግን የሁለተኛው ፅንስ የደም አይነቱ Rh positive ከሆነ ወደ ፅንሱ በማለፍ የፅንሱን Rh positive የቀይ የደም ህዋሶች ያጠቃሉ ማለት ነው፤ ይህም ፅንሱን ለተለያየ አደጋዎች ሊያጋልጠው ይችላል።
ሾትላይ በፅንስ ላይ የሚያስከትላቸው ችግሮች
- በፅንሱ የተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ውሃ መቋጠር
- በፅንስ ላይ የደም ማነስ
- በተደጋጋሚ ፅንስ መጨናገፍ
- ፅንሱ በማህፀን ውስጥ እንዳለ ጊዜው ሳይደርስ ህይወቱ ማለፍ
ሕክምና
- Anti D የተባለ ኢሚውኖግሎቡሊን (immunoglobulin) መድሃኒት በመውሰድ ሾተላይን መከላከል ይቻላል
- Anti D የተባለ መድሃኒት የሚሰጠው በ7ወር እና ፅንሱ በተወለደ በ72 ሰዓት ውስጥ በመስጠት የሾተላይ በሽታን መከላከል ይቻላል።
ወደ ሐኪምየሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን
የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን በየትኛው የእድሜ ክልል ዉስጥ ያለ ሰው ላይ ሊያጋጥም ይችላል።
ምክንያት
- መፀዳጃ ቤት በአግባቡ አለመጠቀም
- የግብረስጋ ግንኙነት በተደጋጋሚ ማድረግ ባክቴሪያ ወደ ዉስጥ እንዲገባ ያደርጋል።
- የስኳር በሽታ እና ሌሎች ተጓዳኝ በሽታወች
ምልክት
- ሽንት በሚሸኑ ጊዜ የማቃጠል ስሜት
- በተደጋጋሚ የሽንት ስሜት መኖር እና ማጣደፍ
- ከሸኑ በኋም የሽንት ፊኛ እንደሞላይ አይነት የዉጥረት ስሜት
- የሽንት ቀለም መቀየር፣ ደም የቀላቀለ፣ ሽታ ያለው ወይም ጥርት ያላለ መሆን
- ኢንፌክሽኑ ወደ ኩላሊት ከፍ ያለ ከሆነ የማስመለስ፡የወገብ ህመም፡ ትኩሳት ይኖራል
ሕክምና
- የበእርግዝና ጊዜ የሚሰጠው ህክምና ለእርግዝና ተስማሚ የሆነ የፀረ ባክቴሪያ መድሃኒቶች
በእርግዝና ላይ የሚያመጣቸው ችግሮች
- በእርግዝና ጊዜ ወደ ኩላሊት ኢንፌክሽን የመቀየር እድል ይኖረዋል
- የሚወለደው ልጅ ላይም ያለ ጊዜው የመወለድ እንዲሁም አነስተኛ የሰዉነት ክብደት ይዞ ሊወለድ ይችላል
መከላከል
- ሽንት ይዞ አለመቆየት
- በቂ የሆነ ፈሳሽ መውሰድ በተለይም ዉሃ
- ከግብረስጋ ግንኙነት በኋላ ሽንት ማሶገድ
- የመራቢያ አካል ዙሪያ ከበድ ያሉ የንፅህና መጠበቂያ ሳሙና አለመጠቀም
ወደ ሐኪም