logo

የወሊድ ዓይነቶች እና ልዩነቶቻቸው

እያንዳንዱ ልጆችን የመውለድ ዘዴዎች የራሱ ጥቅሞች, አደጋዎች እና ግምትዎች አሉት. የወሊድ ዘዴ ምርጫ እንደ የሕክምና ታሪክ, የግል ምርጫዎች እና ባህላዊ እምነቶች ላይ ሊወሰን ይችላል

የተለመደ (Normal) ምጥና ወሊድ

ምጥ በተወሰኑ የጊዜ ልዩነቶች ተደጋግሞ   የሚመጣና እየጨመረ የሚሄድ የማህጸን መኮማተር መኖርና ተያይዞም የማህጸን ጫፍ  መለጠጥ በስተመጨረሻም የጽንሱና እንግዴ ልጅ መወለድ ሂደት ነው።

የምጥ ሂደት

  • ሀ. የመጀመሪያ ደረጃ: ይህ ደረጃ የሚጀምረው በመኮማተር መጀመሪያ ሲሆን የማኅጸን ጫፍ ሙሉ በሙሉ ሲሰፋ (10 ሴንቲሜትር) ሲጠናቀቅ ያበቃል.
  • ለ. ሁለተኛ ደረጃ: በዚህ ደረጃ, ህጻኑ በወሊድ ቦይ ውስጥ ተገፍቶ ይወልዳል.
  • ሐ. ሦስተኛው ደረጃ፡- ይህ ደረጃ በእርግዝና ወቅት ለህፃኑ የተመጣጠነ ምግብ የሚሰጠውን የእንግዴ መውለድን ያካትታል.

bf

በሕክምና ምክንያት ቀዶ ህክምና(ceserean section)ማዋለድ ያለብን መቼ ነው?

  • የማህጸን በበቂ ሁኔታ መኮማተር እያለ ምጡ ከረዘመ)
  • ከዚ በፊት የነበረ የማህጸን ጠባሳ ካለና ምጥ ለመሞከር ቅድመ ሁኔታዎችን ማታማላ ከሆነ
  • የእናቲቱ የዳሌ ቅርጽ የተስተካከለ አለመሆን ወይም መጥበብ( contracted pelvis)
  • የጽንሱ አመጣጥ ትክክል አለመሆን(malpresentation, malposition)
  • የጽንሱ ክብደት >4.5kg ከሆነ
  • የሽርት ውሃ መደፍረስና የጽንሱ የልብ ምት አስተማማኝ አለመሆን (NRFHRP)
  • እትብቱ ከፊት ቀድሞ ከመጣ(cord prolapse or presentation)

በቀዶ ህክምና (ceserean section) ከተወለደ በኋላ ለቁስሉ ምን አይነት ጥንቃቄ ማድረግ አለብት?

  • ቁስሉ ንጹህና ደረቅ መሆን አለበት። ከሻወር በሃላ በንጹህ ጨርቅ ወይም ፎጣ ማድረቅ
  • ቦርጭ ካለ ቁስሉን እንዳይሸፍነው ከፍ አድርጎ ማሰር
  • በቁስሉ ላይ ጫና የሚፈጥሩ ነገሮችን ከማድረግ መቆጠብ (ከባድ እቃ አለማንሳት ፥ ከባድ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አለማድረግ)
  • የህመም ማስታገሻ መድሃኒት መውሰድ
  • ጤናማ አመጋገብ እና በቂ ፈሳሽ መውሰድ ቁስሉ ቶሎ እንዲድን ይረዳል።
  • የኢንፌክሽን ምልክቶች ማለትም ትኩሳት፥ቁስሉ አከባቢ እብጠት፥መቅላት እንዲሁም ከቁስሉ የሚወጣ ፈሳሽ መኖሩን መከታተል።

ማስታወሻ: ወላጆች ስለ ምርጫዎቻቸው ከሐኪሞች ጋር መወያየት እና በግል ሁኔታቸው ላይ በመመስረት በመረጃ ላይ የተመሰረተ ውሳኔ እንዲያደርጉ በጣም አስፈላጊ ነው።

episiotomy(በተለምዶ እስቲች የሚባለው) ምንድነው?

አንዲት እናት በምትወልድበት ወቅት የህጻኑ ጭንቅላት የብልት በር ጋር ደርሶ ያለው ክፍተት ጠቦ ለመውጣት ካስቸገረው የብልት በር ሰፋ ለማድረግ የተወሰነ ይቆረጣል።ከዚያም የእንግዴ ልጁ ሙሉ በሙሉ ከወጣ በዋላ ተመልሶ ይሰፋል።ይህም "episiotomy" ወይም በተለምዶ እስቲች ይባላል።

ከእስቲች በኋላ ምን አይነት ጥንቃቄ መደረግ አለበት?
  • ለብ ያለ ውሃና ጨው በማድረግ በቀን 2-3  ከ10-15 ደቂቃ መዘፍዘፍ
  • ከመጸዳጃ ቤት መልስ በንጹህ ውሀ መታጠብ(ሶፍት መጠቀም አይመከርም)
  • የማያጣብቁ (ሰፋ ያሉ ) የውስጥ ልብሶችን መልበስ
  • በረዶ (ice pack) በቁስሉ ላይ ማድረግ እብጠትና ህመምን ለመቀነስ ይረዳል።